የውህደት ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር፣ አንድ ያገለገለ ቶዮታ ጃፓን ሞዴል LN166L-PRMO5 የተሠራበት ዘመን 1996 የሆነ ፒክአፕ መኪና ባለበት ሁኔታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የተሸከርካሪ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የውህደት ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር፣ አንድ ያገለገለ ቶዮታ ጃፓን ሞዴል LN166L-PRMO5 የተሠራበት ዘመን 1996 የሆነ ፒክአፕ መኪና ባለበት ሁኔታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱ መመሪያዎችን በጥንቃቄ በመከተል በጨረታው መወዳዳር ይችላሉ።

ስለሆነም፤

1. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት (ሀዋሳ) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ተሸከርካሪዉን ሀዋሳ ዋናው መ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ማዬት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚሰጡትን የተሸከርካሪዋጋበተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ቅጽ ላይ መሙላት ይገባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሰጡትን ዋጋ 10 በመቶ በውህደት ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ስም በባንክ የተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ. አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማሰገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለአሸናፊዎች በክፍያ የሚታሰብ ሲሆን፣ ለተሸናፊዎች ግን የጨረታ ውጤቱ እንደተገለጸ የሚለቀቅ ይሆናል።

5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ሙሉ ዋጋ የጨረታው ውጤትበተገለጸ በአስር የሥራ ቀናት ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በተጠቀሰው ቀናት አጠናቆ ገቢ ባያደርግ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

6. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ ከፍሎ እንዳጠናቀቀ ከድርጅቱ ጋር የሽያጭ ውል ይፈራረማል።

7. ሽያጭ እስከ ተከናወነበት ቀን ድረስ በተሸከርካሪው ላይ ያለ ማናቸውም ውዝፍ ግብር ወይም እዳ በድርጅቱ የሚሸፈን ይሆናል። የስም ዝውውርና የ2018 ዓመታዊ ግብሮች በገዢ የሚሸፈን ይሆናል።

8. ተጫራቾች የግዢ መወዳደሪያ ዋጋ ዋናውንበመሙላት በሰም በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ ሀዋሳ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

9. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጧቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል። ተጫራቾች በገዛ ፈቃዳቸው ባይገኙ ድርጅቱ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም።

10 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10.ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0946557281 ይጠቀሙ።

አድራሻ

ሀዋሳ ሕዝብ ማመላለሻ መናኽሪያ ፊት ለፊት ውህደት ትራንስፖርት አክስዮን ማህበር ዋና መ/ቤት

ሀዋሳ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Publishing entity: Wuhedte Transport S.C
  • Bid bond: 10 በመቶ
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published: May 30, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders