የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል Supply, Installation, Configuration and Implementation of Firewall ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/26/2018

1. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል Supply, Installation, Configuration and Implementation of Firewall ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000(አንድ ሺህ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEP Transmission Substation Construction አካውንት ቁጥር 1000252665203 ገቢ በማድረግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ ቤት ሰው ኃይልና ፋይናንስ አስተዳደር ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ትሬዠሪ አስተዳደር ቢሮ ደረሰኙን በማስመራት የጨረታ ሰነዱን ሕንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን Supply, installation, Configuration and implementation of Firewall በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/26/2018 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2 (ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power) ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 የሀገር ውስጥ ግዥ ቢሮ ይከፈታል።

7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-0627 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-15
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-15 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: 350,000.00 /ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: Jun 05, 2026
  • Posted at: 2026-06-05T07:47:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders