የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡- ኢፕድ 025/2018/
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የዳይሪክትሪ መፅሀፍ ህትመት
- ሎት 2. የመፅኄት ህትመት ስራ
- ሎት 3. ኤ4 ወረቀት
- ሎት 4. የፎቶ አክለሪክ ህትመት
ስለሆነም፡-ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዢ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚውል ብር
- ለሎት 1 ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ)
- ለሎት 2.ብር 50,000.00(ሃምሳ ሺህ)
- ለሎት 3 ብር 30,0000.00(ሰላሳ ሺህ)
- ለሎት 4 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።
4. ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አንደኛ ፎቅ አቅርቦት መምሪያ ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 011 156 9869
ኢ.ሜይል procurement@press.et
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-20
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-06-20 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Press Agency
- Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published: Jun 05, 2026
- Posted at: 2026-06-05T08:00:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.