በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል

Description

የሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር 18-2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ

  • የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣
  • የኮስሞቲክስና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
  • የመገናኛ እና የኮምፒውተር ዕቃዎች፣
  • የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
  • የቤት ውስጥ መገልገያዕቃዎች፣
  • ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችንና ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ እና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1.  በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሽጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የሚሰጥ ማስረጃ (ጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ ክሊራንስ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ከተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሌሎች በተ/ቁጥር 1 የተገለጹ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት ሳያስፈልገው ማንነቱን የሚገልጽ ማስረጃ (መታወቂያ) ኮፒ በማቅረብ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፤
  3. ከላይ በተ/ቁ የተገለጸው ተጫራች ማሟላት ያለበት መስፈርት ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከብር 500ሺህ በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሌሎች የተዘረዘሩ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለ ሆኖ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም አያስፈልግም።
  4.  ተጫራቾች ለግልጽ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 4/2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት የዕቃዎችን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፤
  5. ለግልጽ ጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች የሚጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 መግዛት ይችላሉ፤
  6. የግልጽ ጨረታው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 501 ይከፈታል፤
  7.  ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለዕቃ የሰጡትን ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባህር ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲፖዚት አካውንት ቁጥር 1000013088865 ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን የባንክ አድቫይስ ከጨረታ ሰነዱ እና ከሌሎች መረጃዎች ጋር ውስጥ ነው።  በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና አድራሻ በግልጽ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 506 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
  8.  በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዙ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  9. ያስያዙት ዋስትና ለአሸናፊ ተጫራቾች ከሽያጩ የሚታሰብ ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ባሉት ሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ይሆናል፤
  10. የሐራጅ ጨረታው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ ይካሄዳል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው ለዕቃው ከሚሰጡት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት (15%) የሚጨመር ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ 5/በአምስት/ ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፤
  13. ከላይ በተ/ቁ 12 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ማንሳት ያልቻሉ ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ዋትና ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፤
  14. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ውጪ ማድረግ አይችልም፤
  15. ለግልጽ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፤
  16. በጨረታ ከሚሸጡ ተሽከርካሪ ስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያይዞ ሊኖር የሚችል ማናቸውም ወጪ መ/ቤቱ አይሸፍንም፤
  17. በጨረታ የሚሸጥ ዕቃ በተቋሙ ከመወረሱ በፊት የዕቃው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበረ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፤
  18. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ የወጡ ዕቃዎችን ከቅ/ጽ/ቤቱ ሰነድ በመግዛት የወጡ ዕቃዎችን ዝርዝር በመመልከት እንዲሁም በስልክ ቁጥር 0910810163/0910966986 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

 አድራሻ፡- በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው ዘመን ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕርዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-06-12 14:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Bahir Dar Branch Bureau
  • Buyer address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው  የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: በግልጽ ጨረታ 5%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 05, 2026
  • Posted at: 2026-06-05T08:56:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders