Uniforms and workwear
ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት የሰራተኞች ሙሉ ልብስ እና የወንድና የሴት የሥራ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት እና ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 008/2018
ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ አይነት የሰራተኞች ሙሉ ልብስ እና የወንድና የሴት የሥራ ጫማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰፋት እና ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1ኛ በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፣
2ኛ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
3ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4ኛ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5ኛ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
6ኛ በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው።
7ኛ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 ብር /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 26 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
8ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 2% በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
9ኛ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜውን መጥቀስ አለባቸው።
10ኛ ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው።
11ኛ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት (ከሰዓት) ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡00 (ከሰዓት) ታሽጎ በ8፡30 (ከሰዓት) በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
12ኛ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
ስልክ ቁጥር፡- 011 442-1664
ብራና ማተሚያ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-06-18
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት (ከሰዓት)
- Bid opening: 2026-06-18 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡30 (ከሰዓት)
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Branna Printing Enterprise
- Buyer address: ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jun 06, 2026)
- Posted at: 2026-06-06T08:03:53.000Z