የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ትራክተር በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ለእርሻ መካናይዜሽን አገልግሎት የሰጠውን ትራክተር ተከራዮች የኪራይ ክፍያውን በካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሰረት ግዴታቸውን መወጣት ባለመቻላቸው በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ተረክቦ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የተከራይ ስም

ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ

የካፒታል ዕቃ አይነት (Description)

ብዛት

መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚካሄድበት

የሐራጁ ደረጃ

ቀን

ሰዓት

1

አቶ ብርሃኑ ዘላለም አዲስ

 

ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ

 

ትራክተር Brand: NEW HOLLAND, Model: TDSlo, Horse Power:110HP, Origin: TURKEY, Man. Year: 2022

1

4,482,815.50

 

ሃምሌ 1 2018 .

 

3:00-5:00

 

አንደኛ

 

2

አቶ ኑሬ አብደና አቤቱ

 

ደብረማርቆስ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ

 

ትራከተር Brand-LANDINI, Model: LANDFORCE 125, Horse Power: 125HP, Origin: ITALY, Man. Year: 2023

1

6,070,024.91

 

 

7:00-9:00

 

 

3

አቶ ዘላለም ሞላ ታዴ

 

 

ትራክተር Brand LANDINI, Model: LANDFORCE 125, Horse Power: 125HP, Origin: ITALY, Man. Year: 2023

1

6,419,825.92

 

 

9:30-11:30

 

 

የሐራጁ መመሪያ

1 በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከመጀመሩ በፊት ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪል በኩል ቀርቦ መመዝገብ ይኖርበታል።

2. ህጋዊ ሰውነት ያላቸውን አካላት በመወከል በሐራጅ ሽያጩ የሚሳተፍ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ከነማሻሻያዎቹ(ካለ) እንዲሁም የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃዎችን ይዞ ጨረታው በሚካሄድበት በደብረማርቆስ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ መቅረብ ይኖርበታል።

3. ተጫራቾች የንብረቱን መነሻ ዋጋ 1/4 ወይም 25% በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ(CPO) አሰርተው ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ወይም ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል። ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ(CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

4. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል አለበት።ካልከፈለ ባንኩ ሽያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሀራጁ በድጋሚ ይካሄዳል።ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ቀርቦ የዋጋ መቀነስ ከተፈጠረ የዋጋ ልዩነቱን ይሸፍናል።

5. ባንኩ ለሸያጭ የቀረቡትን ንብረቶች እጅ በእጅ በሚደረግ የጥሬ ገንዘብ ሽያጭ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሰራር መሰረት ለመከራየት የሚፈልግ ከሆነ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ በመከፈል የባንኩን የማሽነሪ ዱቤ ግዥ ውል መፈረም ይኖርበታል።

6. ያሸነፈ ተጫራች የሽያጩን 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ የሚከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን የስም ማዘዋወሪያን ጨምሮ የጨረታው አሸናፊው ይከፍላል።አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር የሚታሰብለት ሲሆን ለተሸናፊው ያስያዙት ገንዘብ ይመለሳል።

7. በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (የግለሰብ ተቋም ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የሚጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

8. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነፃ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነፃ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል።

9. ተጫራቾች ትራክተሩ ያለበትን ይዞታ ለማየት ከፈለጉ አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት በቦታው በመገኘት መመልከት ይቻላል።

10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ 058-178-6649

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-08 17:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T08:56:03.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders