በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የህክምና እቃዎች እና የህክምና እቃዎች ጥገና በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር ጨረታ ቁጥር 003/2018 ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የህክምና እቃዎች እና የህክምና እቃዎች ጥገና በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ለመጫረት የምትፈልጉ
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁ
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገባችሁ
3. የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ወይም የዘመኑን ግብር ከፋይ የሆናችሁ
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ
5. ጨረታ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 ብር /ሶስት መቶ ብር ብቻ/
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ብር ሎት 3 አላቂ የህክምና እቃዎች ገንዘብ መጠን 10,000.00፣ የህክምና እቃዎች ጥገና 5,000.00 በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ የተመሰከረለት CPO እና BID BOND ማስያዝ የሚችል ብቻ
7. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ VAT 15% ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ማቅረቢያ ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ቀናት በጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ውስጥ በፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 227 በመግዛት በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች ያሸነፋበትን እቃዎች ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል ውስጥ ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረከብ አለባቸው።
11.ፋይናሻል ኦርጅናል ፋይናሻል ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. ለበለጠ መረጃ ዝርዝር መረጃ ሰነድ ላይ መመልከት ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ከ6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌው ፊት ለፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 126 1509/ 011 126 1961 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የጃንሜዳ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-06-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-19 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Arada Sub City Administration Janmeda Health Post
- Buyer address: ከ6ኪሎ ወደ ጃንሜዳ የሚወስደው መንገድ ከቴሌው ፊት ለፊት አራዳ ክፍለ ከተማ ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T09:28:40.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.