የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የሚኙትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
 ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር DCDE 010/2018

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የሚኙትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይቻላል።

1. ተጫራቾች የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ዴስክ በመምጣት የተሸከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ከግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ/ም ባሉት የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6:30 ከሰአት 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ/ም ሰነድ የሚሸጠው ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት መሆኑን እንገልፃለን።

2. ተጫራቾች ከግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ/ም ባሉት የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ተሸከርካሪዎቹን በአካል ማየት የሚችሉ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹን ለማየት ሲመጡ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን 4ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም።

4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ 20 በመቶ (20%) በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise) ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ብቻ ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመታሸጉ በፊት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ሲፒኦ(CPO) የተሰራው ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።

5. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የግምገማው ውጤት ለተጫራቾች ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ20 የስራ ቀናቶች ውስጥ ሲፒኦ(CPO) ተመላሽ ይደረጋል።

6. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

7. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል።

8. የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተወዳዳሪ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።

9. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናቸው የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ በሻጭ እና በገዥ መካከል ተግባራዊ ይደረጋል።

አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 0633/ 011 896 0623
አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-16
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-16 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defence Construction Design Enterprise
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር አምባሰል ህንፃ ፊት ለፊት የቀድሞው ኖሬላ ግቢ ውስጥ
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ 20 በመቶ (20%)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 07, 2026
  • Posted at: 2026-06-08T12:35:53.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders