ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የካሣ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች፣ የተሽከርካሪ ቅሪት አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን እና የተሸከርካሪ ቅሪት አካላት ለመግዛት የሚፈልጉ ሱማሌ ተራ (ጎበና አባጥጉ መንገድ) ከሚገኘው ዋናው መሥሪያ ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጫረታ ሰነድ በመግዛት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከሲ.አር.ቢ.ሲ በስተቀኝ ወደ ውስጥ በሚያስገባው መንገድ በግምት መቶ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያችን የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ (Recovery) ውስጥ በማየት እስከ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጫረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ቅሪት ንብረቾችን እና ተሽከርካሪዎችን ከ እሁድ ግንቦት 30 ቀን 2018 ጀምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ግቢ ውስጥ እስከ ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ጨረታው ሰኔ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 3:30 ሰዓት ተዘግቶ በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ላይ ይከፈታል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በግሎባል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ወይም (Global Insurance Company S.C) ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸከርካሪዎች ከብር 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) እንዲሁም ለተሸከርካሪ ቅሪት እና ሌሎች ቅሪት አካላት ከብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) ማነስ የለበትም። ከቀረጥ ነፃ ከሆኑት ተሸከርካሪዎች በስተቀር ተሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፈናል። በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉት ማናቸውም ወጪዎች ገዢው ሙሉ በሙሉ ይሸፈናል።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፋበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች እቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጭ ሳይነጣጥሉ በአንድ ጊዜ ከፍለዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርባቸዋል።
- የጫረታ አሸናፊዎች የስም ዝውውር እስከ ስድስት ወር ድረስ ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ጉዳይ ኩባንያው ኃላፊነት አይወስድም።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ስልክ:- 011-156-5851 / 011-126-3385/68 / 011-158-0577
ፋክስ፡- 011-156-2334
Tender details
- Deadline: 2026-06-13
- Bid closing time: 09:30
- Bid opening: 2026-06-13 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Global Insurance S.C.
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 07, 2026
- Posted at: 2026-06-08T12:48:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.