በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የበቆሎ መፍጫ ማሽን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁ.04/2018
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ኦግዲ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዘ ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኝ የቦቆሎ መፍጫ ማሽን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. ጨረታውን የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት – 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲሱ ባስገነባው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይኖርቦታል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10 ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1
|
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ
|
የቦቆሎ መፍጫ ማሽን
|
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰኣት ይከፈታል፡፡
|
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል።
6. የግልጽ ጨረታው መከፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃዉን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርበታል።
9. ከላይ በተ.ቁ 8 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር፡- 022-211-1873/ 022-211-1728 እና 022-211-4010 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ
ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45
- Bid opening: 2026-06-22 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 4፡00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Ministry Of Revenue Adama Branch Office
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 08, 2026
- Posted at: 2026-06-09T07:29:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.