በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከድርጅቱ የሚወገድ ንብረት የብረት ፍቅፋቂ (ችብስ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከድርጅቱ የሚወገድ ንብረት የብረት ፍቅፋቂ (ችብስ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡
2. የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 2% ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታው ሙሉ ሰነድ በኢንዱስትሪው ፋይናንስ ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ::
7. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን አራት ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ትችላላችሁ።
8. ጨረታው ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአራት ሰዓት ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡10 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦላ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 04 66 62 22/ 09 04 66 66 63 ደውለው ቢጠይቁን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4:00
- Bid opening: 2026-06-23 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ 4:10
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Engineering Group New Machine and Spare Parts Manufacturing Industry
- Buyer address: ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሣር ቤት በሚወስደው መንገድ ከኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ያለው ግቢ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: Jun 08, 2026
- Posted at: 2026-06-09T07:48:47.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.