የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የብረታ ብረት ተረፈ ምርቶችን፣ Painting Cane, Carton, Welding Electrode Tips, Old Grinding Disks በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ

ፋብሪካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ ምርቶችን፤ Painting Cane, Carton, Welding Electrode Tips, Old Griding Disks በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች ግለሰቦች ማስረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ቢትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንጻ 4ኛ ወለል በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።

የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ ተረፈ-ብረቶቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል።

ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፣ 251-552 2681/ 251-552 2731

የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-06-22 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Steel Pipe Mill P.L.C.
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Published: Jun 08, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T07:51:02.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders