በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ የደንብ ልብስ የስራ ሴፍቲ አልባሳት እና ጫማዎች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ኬኢኮአመኬፋ 009/2018
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለሰራተኞቹ የደንብ ልብስ የስራ ሴፍቲ አልባሳት እና ጫማዎች በሚፈለገው በጥራትና በብቃት አምርቶ/ሰርቶ ለማቅረብ ልምድ፡ብቃት ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡-
- ነጭ ግዋን በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 140
- ገዋን በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 56
- ቱታ በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 66
- ሸሚዝና ሱሪ በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 332
- ኮትና ሱሪ በቴትረን 6000/ተመሳሳይ ጨርቅ ብዛት 90
- የወንዶች ሸሚዝ ብዛት 104
- ካኪ ቱታ ብዛት 200
- የወንዶች ቆዳ ጫማ/ቡት/ ብዛት 169
- የወንዶች አጭር ቆዳ ጫማ ብዛት 226
- የሴቶች ቆዳ ጫማ አይነት 1 ብዛት 48
- የሴቶች ቆዳ ጫማ አይነት 2 ብዛት 31
- የወንዶች ፕላስቲክ ቦት ጫማ ብዛት 70
- የወንድና የሴት ሴፍቲ ጫማ ብዛት 172 + 18
- የተለያዩ ግላቮች እና የሴፍቲ እቃዎች ብዛታቸው በጨረታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን ከሀገር ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት እና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ናሙና ከቴክኒካል አፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል ኦፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡00 ይዘጋል።
- ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በ4፡30 በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያግደም። ቴክኒካል ምዘና ናሙና ፍተሻ በድርጅቱ በራሱ ይከናወናል።
- እያንዳንዱ ናሙና ተፈትሾ ቴክኒካል ምዘና ያለፉት ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት በአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያግደም።
- አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ ቁጥር 011 554 5771/ 09 20 93 53 36
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ
መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-06-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-06-23 10:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: በኬሚካል ኢንዳስትሪ ኮርፖሬሽን- የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ (ኬኢኮ-አመኬፋ)
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 09, 2026
- Posted at: 2026-06-09T08:31:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.