የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች መካከል የተወሰኑትን ቤቶች በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የ6ኛ ዙር ቤቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ገ.ጨ/አገ/14/10/2018
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ቤቶች መካከል የተወሰኑትን ቤቶች ጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/14/10/2018 መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤቶች ሽያጭ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልከቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው።
4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ከሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ11 ፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ አዳራሽ ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ወይም ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-855-3612 ወይም 011-855-3617 / 09 11-80-92-63 ወይም 09 13-35 62-32 ደውሱ መጠየቅ ይቻላል።
ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et
የፖሳቁ . P.O. Box 299
ፋክስ ቁጥር: 011-554-6045/ 011-552-4646
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-06-19
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-06-19 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰአት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jun 09, 2026
- Posted at: 2026-06-09T08:46:09.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.