ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ እቀዎችን የኤሌክትሪክ አቃዎች ባለ 36 እና 18 ዋት፣ የታንቡራታ የእንጨት በር፣ ጅብሰም ቦርድ ቁርጥራጭ፣ የእንግዳ ወንበር፣ የአልሙንየም ቁርጥራጮች፣ ልዩ ልዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ መስታዎቶች፣ የሞራሌ ቁርጥራጭ እንጨቶች፣ የዲሽ ሳህኖች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ እቀዎችን የኤሌክትሪክ አቃዎች ባለ 36 እና 18 ዋት፣ የታንቡራታ የእንጨት በር፣ ጅብሰም ቦርድ ቁርጥራጭ፣ የእንግዳ ወንበር፣ የአልሙንየም ቁርጥራጮች፣ ልዩ ልዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ መስታዎቶች፣ የሞራሌ ቁርጥራጭ እንጨቶች፣ የዲሽ ሳህኖች እና የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አጫርቶ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች በማሟላት መጫረት ይችላሉ።

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ፡-

1. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣

2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል 2ኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል።

3. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርበታል።

4. ተጫራች በጨረታ ሰነዱ የተያያዙ እቃዎች ኮድ 1፣ ኮድ 2፣ ኮድ 3፣ የእቃዎችን ዝርዝር በማየት ለእያንዳንዳቸው ለየብቻ የሚገዙበት ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።

5. ተጫራች አሸናፊ መሆኑን በስልክ ከተነገረው እና ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ወደ ድርጅቱ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ ክፍያውን ከፍሎ እቃዎቹን በተጠቀሱት ቀናት ማንሳት ይኖርበታል።

6. ተጫራች ጨረታውን አሸናፊ መሆኑን ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ክፍያውን ከፍሎ እቃዎቹን ለማንሳት በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሱት የሥራ ቀናት ውስጥ ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆን ቢቀር ያስያዘው CPO ለይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሂሳብ ገቢ ይሆናል።

7. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 8 (ስምንተኛው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8 (ስምንተኛው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል።

9. ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ የታሸገ ሲሆን፣ በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት መግለጽ ይኖርበታል።

10. ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል።

11. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላል።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ፊት ለፊት ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ስልክ ቁጥር፡- የቢሮ 011 558 0129/011 557 6954

ማሳሰቢያ፡- ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-06-17
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 (ስምንተኛው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-17 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 (ስምንተኛው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yiha Real Estate P.L.C.
  • Buyer address: ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 09, 2026
  • Posted at: 2026-06-09T09:02:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders