ወላይታ ልማት ማህበር ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ በግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የቤት ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ወላይታ ልማት ማህበር የቤት ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር ወልማ/002/2026 ወላይታ ልማት ማህበር ማህበሩን ለማጠናከር በመካሄድ ላይ በሚገኘዉ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን (ወላይታ ሶዶ ከተማ ቦዲቲ እረካ'ጠበላ በሌአዋሳ'ዲምቱ ጋራጎዶ ሄምቤቾና ጎጮ) ከተሞች የሚገኙ ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ በግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በጨረታ የሚሳተፉ ግለስቦች ከሆኑ ህጋዊ መታወቂያ፣ ድርጅቶች ከሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ህጋዊ የመታወቂያ ካርድ ህጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸዉ መሆን አለባቸው።
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን ወላይታ ሶዶ ከሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል እና የወላይታ ልማት ማህበር ቤቶቹ ለጨረታ በወጡባቸዉ ከተሞችና ወረዳ አስተዳደሮች በሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10% ለቤቱ ሽያጭ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋ መሰረት በማናቸውም ንግድ ባንኮች የተመሠከረለት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሠራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር አያይዘው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዕለቱ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት ታሽጎ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9፡15 ሰዓት ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል በይፋ ይከፈታል።
- 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ቤት ኮድ በመምረጥ የመጫረቻ ሰነዳቸዉንና ዋጋ ማቅረቢያውን ሳይዘለል፣ ሳይታለፍ ስርዝ ድልዝ ሳይገኝበት በሙሉ አጠናቅቆ በመሙላት ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በሰም በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
- የጨረታው ሃደት የሚከናወነው ተጫራቹ መግዛት ለሚፈልገው ቤት ያቀረበዉን ጠቅላላ ዋጋና ሰነዶችን መሰረት በማድረግ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መግባት የሚኖርበት ሲሆን ይህን ካልፈጸመ ጨረታውን በፈቃዱ እንደሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቹ በጨረታው ማሸነፉን በማስታውቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጨረታ ያሸነፈበትን ቤት ዋጋ በተገባዉ የውል ስምምነት መሰረት ገንዘቡን በማህበሩ አካዉንት ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- በጨረታ ያሸነፉትን ቤቶች ውል ለማጸደቅ፤ስም ለማዛወርና ማናቸውንም ተያያዥ ወጪዎች ገዥዉ ይሸፍናል።
- ተጨራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቤቶቹ በሚገኙበት ከተማ ማህበሩ በሚያመቻቸው ሰዓት ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፣
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም።
- የጨረታ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይፈቀድም።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመቅረብ ወይም ስልክ ቁጥር 09 10 54 19 63/ 09 13 25 57 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ወላይታ ልማት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Publishing entity: Wolaita Development Association
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 08, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.