በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ጎማዎች እና ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ባሉበት ሁኔታና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ተሽከርካሪ ጎማ እና ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ECC-JB0/03/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ንብረትነታቸው የቅ/ጽ/ቤቱ የሆኑ ሎት አንድ ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ጎማዎች ሎት ሁለት ያገለገሉ ፈርኒቸሮች ባሉበት ሁኔታና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ቀርበው በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፣
2. የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
3. ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሰነድ ገዝተው እቃዎችን በጅግጅጋ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ተገኝተው መመልከት ይችላሉ፣
4. ተጫራቾች በሚገዙት ዕቃዎች የጨረታ የመሸጫ መነሻ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በሚዘጋበት ቀን እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ጠቅላላ የሎት ዋጋ እና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን መስፈርቶች አሟልቶ መገኘት ነው፣
6. የሎት የመሸጫ የመነሻ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) ያስያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች መስፈርቶችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፤
7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል፣
8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚዘጋና የሚከፈት ሲሆን ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዉል መፈረም እና ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
10. ቅ/ፅ/ቤቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በሥሙ ወይም በህጋዊ ተወካዩ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ በ10 ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህ መሆን ካልቻለ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡ ዕቃውም በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0915 748 790 ወይም 0913 220 473 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን መቀበል ወይም አለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻችን፡- ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 05
ተጨማሪ መረጃ ፡-በስልክ ቁጥር 0915 748 790 ወይም 0913 220 473
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-24
- Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 10, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.