የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር የተለያዩ የተማሪ መማሪያ መፅሐፍቶችን ለማሳተም ይፈልጋል
Description
የመፅሐፍ ህትመት ጨረታ
ማስታወቂያ (OPSA/001/2018)
የኦሮሚያ የግል ት/ቤቶች ማህበር ለ2019 የት/ርት ዘመን የሚያገለግሉ የተለያዩ የተማሪ መማሪያ መፅሐፍቶችን ከኦሮሚያ ክልል ት/ቢሮ በተቀበለዉ ስፔስፍኬሽንና ሶፍት-ኮፒ መሰረት ለማሳተም የሀገር ዉስጥ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
የጨረታ ሁኔታ
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች በግድ ማሟላት ይጠበቅባችኋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የ2017/2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ቄራ አካባቢ ከሚገኘዉ የማህበሩ ጽ/ቤት (ሳንቴ ክሊንክ አጠገብ ወይንም የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ህንፃ ቢሮ ቁጥር-104) ይህ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በተራ- ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 500 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከዚህን በፊት ከማህበሩ ጋር መልካም የሥራ ግንኙነት የነበራቸዉ ወይንም ማህበሩን ላልተገባ እንግልት፣ ኪሳራ፣ የህትመት ጥራት ብልሽት ወይንም መጓተት ያላዳረጉ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በወርኮሾፖቻቸዉን የሚገኙትን የማተሚያ ማሽኖች ይዞታ፣ የሰዉ ሀይል አደረጃጀት እና የሥራ ልምዶቻቸዉን ለማህበሩ ሠራተኞች እና የቦርድ አባላት የማሳየት ፍቃደኛ ስለመሆናቸዉ በፅሑፍ መግለፅ ይጠበቅባችኋል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ለእያንዳንዱ መፅሐፍ ከነቫቱ በመተመን ከማህበሩ ባገኙት የፋይናንስ ሰነድ ላይ ምንም ዓይነት የቅፅና የስፔስፍኬሽን ለዉጥ ሳያደርጉ ዋጋቸዉን በእስክሪብቶ በመሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መመለስ አለባቸዉ፡፡ በኤንቬሎፖቹ ላይ የጨረታ ቁጥር፣ የአጫራች ስምና አድራሻ፣ የተጫራቹ ስምና አድራሻ፣ የፕሮጄክቱ ስም ወ.ዘ.ተ በትክክል መፃፍ አለባቸዉ፡ የሰነዶች መመሰቃቀልና መዛባት ከዉድድር ያሰናብታል። ማስከበሪያ ዋስትና ወይንም ቢድ ቦንድ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 1% (አንደ በመቶ) በሲፒኦ/CPO/ ወይንም በቅድመ-ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና / unconditional bank guarantee/ ማቅረብ ይኖርባችኋል። የጨረታ ማስከበሪያ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምረዉ በ11ኛዉ ቀን (ቅዳሜ 13/10/2018) ጠዋት እስከ 4፡30 ድረስ ብቻ ለማህበሩ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸዉ። ጨረታዉ በዚሁ ዕለት 5፡00 ላይ በማህበሩ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከተረጋገጠ እና ህጋዊ ዉል ከተዋዋሉ ቀን ጀምሮ ሥራዉን በ30 ቀናት ዉስጥ የማስረከብ ግዴታ ይገባሉ። የዉል ማስከበሪያ 10% (አስር ከመቶ) በቅድመ-ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee/ ያስይዛሉ።
- ተጫራቾች ያላቸዉን አቅም ከግምት ዉስጥ በማስገባት ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል መወዳደር ይችላሉ።
- አሸናፊ ተጫራቾች ሥራዉን ለመጀመር ቅድመ-ክፍያን/advance payment/ እንደቅድመ-ሁኔታ መጠበቅ አይችሉም:: የቅድመ-ክፍያ መጠን በዉሉ ላይ የሚጠቀስ ሆኖ አፈፃፀሙም በዉሉ ላይ በሚጠቀስ መስፈርት መሠረት ይሆናል።
- ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለዉ።
ለበለጠ መረጃ፡ 0913-490944/ 0905-050887
Tender details
- Deadline: 2026-06-20
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-06-20 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Private School Association
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500 ብር
- Published: Jun 10, 2026
- Posted at: 2026-06-10T10:32:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.