Disposal, scrap and surplus sales
የኮ/ቀ/ክ/ወ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚወገዱ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የተለያዩ አልባሳት፣ የተለያዩ መገልገያ እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ወ-01-01-/2018
- ሎት1 የሚወገዱ ቁርጥራጭ ብረቶች
- ሎት2, የተለያዩ አልባሳት
- ሎት3 የተለያዩ መገልገያ እቃዎች
ከላይ በዝርዝር የተገለጹትን እቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች በጨረታ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና ሰነድ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መያያዝ አለባቸው።
- ከአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መረጃቸው መገኘት የሚችል።
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚፈልጉትን በሙሉ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናት ውስጥ ቦታው ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት1 ብር 6,000/ስድስት ሺህ ብር/ሎት2 ብር 5,000/አምስት ሺህ ብር ሎት3 ብር 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO ብቻ በየሎቱ በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላል።
- አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ አቅራቢዎች የጨረታውን ሰነድ ወደ አየር ጤና በሚወስደው መንገድ ከዘነበ ወርቅ አደባባይ ከፍ ብሎ የሚገኘው ወረዳ 01 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት አራተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 402 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በ11ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የማይሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን ና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለትበፖስታ ላይ በመፃፍ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውሰጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ባሉት 10 የሥራ ቀናት ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወረዳው በር ላይ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል በተጠቀሰው ቢሮ ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ካላንደር የሚዘጋው ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተጠቀሰው ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚገዙበት ወቅት ሰነድ የሚሸጠው መሆኑን ማወቅ አለባቸው
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ7(ሰባት) የሥራ ቀናት በኋላ የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል መዋዋል አለበት ካልቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ፡- በስልክ ቁጥር 011-348-66-08 /01–3-69-42-06
የኮ/ቀ/ክ/ወ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-22 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration Office 01 Finance Economic Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jun 11, 2026)
- Posted at: 2026-06-11T07:47:51.000Z