የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሥራና የአደጋ መከላከያ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ብ.ግ./ኢ.ኢ.ኮ/08/2018

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሥራና የአደጋ መከላከያ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናችውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቤ ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ጫማዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 40,000.00 ብር /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ማቅረብ ይችላሉ። ከኢንሹራንስና ከፋይናንስ ተቋማት የሚቀርቡ ዋስትናዎች ተቀባይነት የላቸውም። ስለዚህ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲዲ ኮፒ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

5. ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።

7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው።

8. ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል (አደይአበባ ስታዲየም) በሚያስገባው መገንጠያ መንገድ አጠገብ አዲሱ መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ

ስልክ ቁጥር፡-+251 11 872 0722

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-23 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Engineering Corporation
  • Bid bond: 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jun 11, 2026
  • Posted at: 2026-06-11T08:38:58.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders