የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባሕርዳር በሚገኘው ዋናው ግቢ ስቶር እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ስቶር የሚገኙ ያገለገሉ ጎማዎች እና የቅየሳ መሣሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ግ/ጨ/ቁጥር 48/2018

የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባሕርዳር በሚገኘው ዋናው ግቢ ስቶር እና ፕላስቲክ ፋብሪካ ስቶር የሚገኙ ያገለገሉ ጎማዎች እና የቅየሳ መሣሪያ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች የሚሸጡትን የቅየሳ መሳሪያ እና ያገለገሉ ጎማዎች ዋናው ግቢ ስቶር እና ፕላስቲክ ፋብሪካ በሚገኘው ስቶር በአካል በመገኘት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሥራ ሰዓት በመመልከት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይቻላል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆነ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ። ነገር ግን በማህበር ለመወዳደር የሚፈልግ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ በፍትህ ተቋም የተሰጠውን ሕጋዊ ውክልና ማቅረብ ይጠበቅበታል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚኘው ቢሯችን ቢሮ ቁጥር 02 ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ማስገባት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /bid bond/ የተጨማሪ እሴት ታክስን 15% ጨምሮ የሚገዙበትን ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በባንክ ማስያዥያ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ ማለትም ቼክ ያስያዘ በጨረታው ውድቅ ይሆናል።

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙትን የጨረታ ማስያዣ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በከፈሉ ማግስት ጀምሮ እቃውን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው። ሆኖም ግን በተባለው ቀን የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት ሲፒኦ ተወርሶ ኮርፖሬሽኑ የሚያዋጣው ከሆነ 2ኛ ለወጣው ተጫራች የሚሸጠው ይሆናል።

8. ጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒልክ ክ/ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሯችን በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ለውኃ ሥራዎች ኮርፓሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000265163223 እና አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ለውኃ ሥራዎች ኮርፓሬሽን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000135939858 ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ አስገብተው ማስረጃ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።

9. ገዥው በተፈቀደለት የጊዜ ገደብ ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ እቃውን መረከብ ባይችል ያጋጠመውን ችግር ከበቂ ማስረጃ ጋር በጽሑፍ አመልክቶ የድርጅቱ የሚመለከተው ኃላፊ ሲፈቅድ ብቻ የርክክብ ጊዜው ሊራዘም ይችላል።

10. የሚሽጡትን የቅየሳ መሳሪያ እና ያገለገሉ ጐማዎች በተመለከተ ማንኛውም የጉልበት ሠራተኛ ወጭ እና የመጓጓዣ ወጭ አሽናፊው ድርጅት የሚሸፍን በመሆኑ በዚህ አግባብ ግዴታ የሚገባ ይሆናል።

11. ለእያንዳንዱ እቃ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ አሸናፊ ሆኖ ይመረጣል።

12. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም። ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው የሚሸጡ ዕቃዎች መጠን ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

14. የሚሞላው ዋጋ ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ጋር በሚያይዘው ሰንጠረዥ መሠረት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን 09-85-07-75-18 እና 09-18-80-06-19 እንዲሁም በኮርፖሬሽናችን ዌብሳይት www.wwc.com.et  እና https://www.facebook.com  ቴሌግራም፡ https://t.me/WaterWorksCorporationOfficial  መረጃ ማግኝት ይችላሉ።

ውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-27 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Water Works Construction Enterprise
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T08:15:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders