የሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ የተለያዩ መድሀኒቶች፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ሠ/ፍ/ጤ/ጣ/ግ/ጨ/003/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

1. የተለያዩ መድሀኒቶች፣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የላብራቶሪ ረኤጀንቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።

1.ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ (አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TlN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4, በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዢዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልጾላቸው ግዴታቸውን የተወጡና መልካም አፈጸጻም ያላቸው እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግዢ መመሪያን በአግባቡ የሚከተሉ እና የሚፈጽሙ፣

6. በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 45 የግዢ ከፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. መ/ቤቱ በሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ በክፍል 6 ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገግሎቶች ዝርዝር መገለጫ ላይ ናሙና /ሳምፕል እንድታቀርቡ በተጠየቀው መሠረት የተጠየቁትን ናሙና ሳምፕል| የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ቢሮ ቁጥር 45 ግዥ የስ/ሂደት እንድታስገቡ እየገለጽን ናሙና (ሳምፕል) ያልቀረበባቸው እቃዎች ውድቅ እንደሚሆኑባችሁ አውቃችሁ ለምትወዳደረበት እቃዎች በሙሉ ናሙና(ሳምፕል) እንድታቀርቡ እያሳሰብን የምታቀርቡትን ናሙና ሳምፕል በተመለከተ ጤና ጣቢያው የራሱን ኮድ የሚሰጥ በመሆኑ በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል/ ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቀ የተከለከለ ነው።

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን ይኖርበታል።

9. ተጫራቾች በሚወዳደረበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% ሁለት /ፐርሰንት/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ለእያንዳንዱ ሎት የምታቀርቡት CPO መጠን እንደሚከተለው ይሆናል።

1. መድሀኒቶች የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች 6214፡- 80,067.71 (ሰማንያ ሺ ስልሳ ሰባት ብር ከ71/100 ሳንቲም ብቻ) ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት የተከለከለ ሲሆን ነገር ግን ይህ ሆኖ ቢገኝ ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ።

10. የጨረታው ዋጋ ለ2 ወር ጸንቶ ይቆያል ይህም ሲሆን ገዥና ሻጭ ተስማምተው እስከ ቀጠሉ ድረስ ለ6 ወራት ድረስ በስምምነት ይቆያል።

11. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በሚመለከት አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባችሁ።

12. ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፒስፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም።

13. ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመሳሽ የምታደርጉ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ስነድ ጤና ጣቢያው የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል።

14. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ወይም ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል:: ካልሆነ ግን እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ፣ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።

15. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣ በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች በጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል።

16. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጤና ጣቢያው ግቢ ቢሮ ቁጥር 45 ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ይታሸግና በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፣ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።

17. በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች በግምገማው እኩል ውጤት ካቀረቡ አሸናፊውን ለመለየት ዕጣ የሚጣል ይሆናል።

18. አሸናፊ ተጫራች የግዢ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ ከደረሰው ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት ውል ከግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት፣ ውል ሰጪ ፈቃደኛ ካልሆነ በቀጣይ ከመንግስት ግዢ እንዲታገድ ይደረጋል።

19. የጨረታ ውጤቱ ይፋ ሆኖ አሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች እንደተለዩ በማስታወቂያ ላይ ከተገለጸ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያሲያዙትን 2% የጨረታ ማስከበሪያ የይመለስልኝ ደብዳቤ በመጻፍ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራች ግን የውል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት ዕቃ አገልግሎት/ ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዢ የውል ማስከበሪያ ሲያሲዙ ቀደም ብለው ያሲያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ 2% ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

20. ገዢው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን /ብዛት/ላይ 20% ከውል በፊት ወይም ከውል በኋላ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።

21. አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀዕው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በክፍል 8 በልዩ የውል ሁኔታዎች ላይ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረክብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል:: በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ 10% መ/ቤቱ ይወርሳል -

22. በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል።

23. በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሚ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ በ ሁለት ቀናት ውስጥ መልስ እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡ ሆኖም በተሰጠሙ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም።

24. በውድድር ወቅት በአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በአንዱ ዋጋ መሰረት እና በአሃዝና በፊደል በሚገለጽበት ወቅት ልዩነት ቢኖር በፌደል በተገለጸው መሰረት በማስተካከል ይገመግማል።

25. ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና/ሳምፕል/ በሚመረመርበት ወቀት በራሱ ተፈጥሮ ቢጠፋ ወይም ቢበላሽ መ/ቤቱ ካሳ አይከፍልም።

26. ያቀረቡት ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60/ስልሳ ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲወስዱ ተገልጾላቸው ጠይቀው ካልወሰዱ ለመንግስት በውርስ ገቢ ይደረጋል።

27. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስትርት/ወጪ/ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ በተጨማረም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

28. በጨረታው ሠነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች አስመልክቶ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ በጽሁፍ ሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 45 በአካል በመምጣት ማቅረብ /መጠየቅ / ትችላላችሁ።

29. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አቃ/ቃ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሠሳም ፍሬ ት/ቤት አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 4340351
ሠላም ፍሬ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:30
  • Bid opening: 2026-06-24 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ይታሸግና በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ
  • Buyer address: አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ3 ሰላም ፍሬ ት/ቤት አጠገብ
  • Bid bond: 2% ሁለት /ፐርሰንት/
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T08:15:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders