ድጋሚ የወጣ የተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሃ/የተ/የህ/ስ/ማ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ዳግማዊት ሙሉጌታ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/0061/2017 በ13/7/2017 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/108367 በ28/11/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ለማስፈጸም ለኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የተሽከርካሪ ማቆሚያ ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B35722 አ.አ ሊፋን የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመገኘቱ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 108367 በ13/09/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 137,500 (አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-06-30 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 12, 2026
  • Posted at: 2026-06-12T08:26:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders