የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የመድኃኒት አቅርቦት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል በመዋዋል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር RE-LP/OT/23/SIG/2018

1. የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እና የሰራተኛ ቤተሰቦች የመድኃኒት አቅርቦት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል በመዋዋል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ህጋዊ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ) ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin No.) ሠርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ የሚመለከተው የመንግስት አካል ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪ ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (ብር አምስት መቶ) በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000888862 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ
ግዥና ንብረት አስተዳደር መምሪያ
ሜክሲኮ አካባቢ ከሚገኘው አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ፊት ለፊት፣ ፈሊፒስ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 220
ስልክ ቁጥር +251 11 551 6271 ወይም 011 550 0417 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 3 በተገለፀው አድራሻ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) በክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለስልሳ (60) ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

7. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለሰላሳ (30) ቀናት ይሆናል።

8. ግሩፑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-24 14:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
  • Buyer address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
  • Bid bond: 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 13, 2026
  • Posted at: 2026-06-13T07:11:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders