የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-

  • ሎት 1 ብረታ ብረት
  • ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 3 የተሽከረካሪዎች ጎማ
  • ሎት 4 የእንጨት ውጤቶች
  • ሎት 5 የጨርቃ ጨርቅና ጫማ
  • ሎት 6 የተለያዩ ጠርሙዝና ገበቴዎች
  • ሎት 7 ግሬደር ማሽን
  • ሎት 8 ትራክተር ከነጋሪው
  • ሎት 9 የመስክ መኪና
  • ሎት 10 ሞተር ሳይክል

1. ዕቃዎቹ ያሉበት ፡- አድራሻ ሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት ሆሳዕና ከተማ ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎቶች ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።

2. ማንኛውም ተጫረቾች በጨረታ ለይ መሳተፍ ይችላል።

3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10/አስር/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ዕቃዎች በተናጠል፡- ከሎት-1 እስከ ሎት 6 ድረስ ለተገለፁት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ እና ከሎት 07 እስከ ሎት 10 ድረስ ለተገለፁት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ በሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈል ከሆሳዕና ከተማ ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 011 የፋይዳ መታወቂያ ይዞ በአካል በመቅረብ ዘወትር ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ዕቃዎች(ንብረቶች) በሎት ወይም በከፊል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ ተቋሙ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና እና ሁለት ኮፒ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ እንደገና ሦስቱም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም በማሸግ ዘዉትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 011 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸዉ።

6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባት ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።

7. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል ፊርማ የሌለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀበይነት አይኖረዉም።

8. ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ዕቃዎች(ንብረቶች) የጨረታ ዋስትና ካስያዙት ንብረቶች /ዕቃዎች/ ውጪ መወዳደር አይቻልም።

9. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ሎት መጫረት ይችላሉ።

10. ተጫራቾች ጨረታው ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው /አስር አንድኛው/ ቀን ከጧቱ 3፡30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የሥራ ቀን ከልሆና በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

11. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ንብረቶች /ዕቃዎች/ አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለጸበት 10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።

12. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።

13. አሸናፊው ተጫራች የተሽከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።

14. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።

15. ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይፈቀድም።

16. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0916 838 549 / 0910 097 563 / 0926 118 263 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-23
  • Publishing entity: Hosana City Administration Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Jun 13, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders