በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

 የጨረታ ማስታወቂያ 003/2018

በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የህክምና መድኃኒቶች እና ሪኤጀንቶች ግዥ

በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር መኖራቸውን ማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የቫት ተመዝጋቢና ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከጤና ጣቢያው ግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  4. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ በፖስታ በማሸግ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናል እና ኮፒ እሽግ ለያይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ኮፒ የለሌው ኦርጅናል ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
  5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
  6.  ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ6ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል።
  7.  የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ጤና ጣቢያው ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  8. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን፡- በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ቤላ ወይም ጣሊያን ኤምባሲ ጎን የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ

እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ

ስልክ ቁጥር 09 13 60 56 32 ወይም 09 13 66 67 47

በየካ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት

የእንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-19
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ6ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00
  • Bid opening: 2026-06-19 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ6ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Entoto No.1 Health Post
  • Buyer address: ልዩ ስሙ ቤላ ወይም ጣሊያን ኤምባሲ ጎን
  • Bid bond: 3,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር በየሎቱ
  • Published: Jun 13, 2026
  • Posted at: 2026-06-13T08:20:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders