ጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የማይጠቀምባቸውን የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ ተሽከርካሪዎች፣ የቢሮ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተለያዩ ኬሚካሎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2018

ተቋማችን ጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ የማይጠቀምባቸውን የተለያዩ ብረታ ብረቶች፤ ተሽከርካሪዎች፤ የቢሮ እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተለያዩ ኬሚካሎች አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ከላይ ለተገለጹት ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት እና የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በመንግሥት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ -ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመከፈል በተቋማችን ጋፋት አርማመንት ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግብይትና ሽያጭ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 20 የሥራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈጸመበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት ክፍያ በመፈፀም በ20 ቀናት ውስጥ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

7. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ21ኛ (ሃያ አንደኛው) ቀን 4:30 ላይ ይከፈታል። የመከፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ይከፈታል።

8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም። ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- +251-11 433 8822 / +251 92 001-7838 

አድራሻ ኡዴ ደንካካ 7.5 ኪ.ሜ ፒስታ መንገድ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ጋፋት አርማመንት ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 20 የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-07-07 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ21ኛ (ሃያ አንደኛው) ቀን 4:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Gafat Armament Engineering Industry
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Jun 13, 2026
  • Posted at: 2026-06-13T09:13:34.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders