የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ መኪኖች፣ ያገለገሉ ጎማ፣ የተሰባበሩ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች እና ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት አገልግሎት የማይሰጡ መኪኖች፣ ያገለገሉ ጎማ፣ የተሰባበሩ የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች እና ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ።

1. ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ በክልሉ በሚገኙ ሆሳዕና፤ ወልቂጤ፣ ቡታጅራ እና ዱራሜ ከተሞች ሲሆን ዝርዝር አድራሻ መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጸዋል።

2. በጨረታው ላይ የሚወዳደር ማንኛውም ተጫራች ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል።

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 (ሃያ) ቀናት ለእጩ ተወዳዳሪዎች ከፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመክፈል ከቢሮው መንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ከንብረት ዋጋ ጥናትና ማስወገድ ዳይሬክቶሬት ከፍል በመንግስት የስራ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።

5. ንብረቶቹን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት ጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ባሉበት ቦታ ተገኝቶ ማየት ይቻላል።

6. ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጂናልና ኮፒ ዶክመንቶችን በመለየት በጥንቃቄ ለየብቻ በኢንቨሎፕ ፖስታ በማሸግ እስከ 20ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7. ጨረታው በ20ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራች በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ በመቅረቱ የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም።

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/ CPO/ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ስም አዘጋጅተው ከመወዳደሪያ ኦርጂናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

10. አሸናፊው እንደታወቀ ለተሸናፊው ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ CPO ተመላሽ ይደረግለታል።

11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 09 13 73 53 67 / 09 10 92 89 86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-02
  • Publishing entity: የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 13, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders