የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 014/18

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 ከአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አዲስ አበባ ዋና ግቢ እና ደብረዘይት ሥልጠና ማዕከል በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በኢንስቲትዩቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።

6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡

8. ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡

9. ኢንስቲትዩቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡

10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

11. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ሕንፃ

የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-29 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Management Institute (EMI)
  • Buyer address: ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T07:52:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders