በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ንብረት የሆነው ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ በዘርፉ በተሰማሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ ጥገና ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፖሊስ መምሪያ ንብረት የሆነው ቶዮታ ላንድ ክሩዘር ተሽከርካሪ በዘርፉ በተሰማሩት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
- ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፤
- በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፤
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 15 ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-131-01-08 መደወል ይችላሉ።
በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብረት አስተዳደር
ዳይሬክቶሬት - ዲላ
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Publishing entity: በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Jun 14, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.