መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰነድ ቁጥር 125
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ቁሳቁሶቹም፡
- የተለያዩ ብረታ ብረቶችና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች (ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ)
- ከእንጨትና ከብረት የተሰሩ ወንበሮች
- ከብረት የተሠሩ ቋሚ የመብራት ፖል (ምሰሶዎች) ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
- ያገለገሉ ስፕሪንግ ፍራሾች ናቸው።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾ አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲፒኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
ጨረታው ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 30-79-64-13 ወይንም 09 75-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-06-22 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ በ5፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mekedonia Charity Association
- Buyer TIN: 0027054421
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: Jun 14, 2026
- Posted at: 2026-06-15T08:12:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.