የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች(መኪናዎች፣ ትራክተሮች፣ ተጎታች ጋሪ፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌት) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች(መኪናዎች፣ ትራክተሮች፣ ተጎታች ጋሪ፣ ሞተር ሳይክሎች እና ብስክሌት) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-

  • ሎት-1 መኪናዎች
  • ሎት-2 ትራከተሮዎች
  • ሎት-3 ተጎታች ጋሪዎች
  • ሎት-4 ሞተር ሳይክሎች
  • ሎት-5 ብስክሌት

1. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ እና ሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።

2. በተሽከርካሪዎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።

3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል፡- ሎት-1 መኪና ብር 400.00/አራት መቶ ብር/ ፣ ሎት-2 ትራክተር ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ፣ ሎት-3 ተጎታች ጋሪ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ፣ ሎት-4 ሞተር ሳይክል ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ እና ሎት- 5 ብስክሌት ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና/Original/ እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።

7. ተጫራቾች ለመግዛት የፈለጉትን ተሽከርካሪ/ዎች የጨረታ ዋስትና ካስያዙት ተሽከርካሪ/ዎች ውጪ መወዳደር አይቻልም። 

8. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ።

9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው /አስራ አንድ/ ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ5፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

10. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10/አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።

11. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል። 

12. አሸናፊው ተጫራች የተሸከርካሪ ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል። 

13. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።

14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046-555-2337 / 2316 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-24
  • Publishing entity: Hadiya Zone Finance Bureau
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Jun 14, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders