ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሽከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን የካሳ ክፍያ ፈፅሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎች እና የተሸከርካሪ አካላት ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ንብረቶቹን መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቆርኪ ፋብሪካ ወደሚድሮክ ተርሚናል በሚያልፈው አስፋልት መንገድ ገብቶ አሉሙኒየም ፋብሪካ ፊት ለፊት በስተቀኝ በኩል በሚገኘው የኩባንያችን የከባድ ተሽከርካሪዎች ጊዜያዊ ማቆሚያ ስፍራ እና ቃሊቲ ቆርኪ ፋብሪካ ጀርባ መድን ዲኮር አጠገብ በሚገኘው የቀላል እና መለስተኛ ተሽከርካሪዎች ጊዜያዊ ማቆሚያ ስፍራ (የኩባንያችን ሪከቨሪዎች) ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በቦታው በመገኘት እና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ደንበል ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር SFS-211 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው ማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ደንበል ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር SFS-211 ውስጥ ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀርበው ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ሲሆን የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋቸው ከብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ከ00/100) በላይ ለሆኑ ንብረቶች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋን 10% (አስር በመቶ) እንዲሁም የጨረታ መነሻ ዋጋቸው ከብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ከ00/100) በታች ለሆኑ ንብረቶች ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ከ00/100) በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ኢማ ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታው ለተካተቱ ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማናቸውም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።
- የጨረታ አሸናፊዎች የመክፈያ ቀናቶች ኩባንያው የጨረታ ውጤቱን ካሳወቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት የስራቀናት ድረስ ብቻ ሲሆን አሸናፊዎች ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤቱ የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
- ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማስታወሻ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 553 5129 / 011 553 5130 ይደውሉ
ንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
Tender details
- Deadline: 2026-06-22
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-06-23 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Nile Insurance Company S.C.
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published: Jun 14, 2026
- Posted at: 2026-06-15T11:19:27.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.