የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ እና በቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ያሉትን ያገለገሉ እቃዎች እና የማዕድን ተረፈ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር RE-EMC/OT/NCB/01/2018

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ እና በቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ያሉትን ያገለገሉ እቃዎችእና የማዕድን ተረፈ ምርቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

ብዛት

የመጫረቻ ሰነድ የሚቀርብበትና የሚዘጋበት የመጨረሻ

የመጫረቻ ሰነድ የሚከፈትበት

ቀን

ሰዓት 

ቀን

ሰዓት 

1

Gelophany grease KAUS- 45,

166 barrel

23/10/2018

4:00

23/10/2018

4:30

2

ፔሪዶት (peridoite)

3267kg

23/10/2018

4:00

23/10/2018

4:30

3

Gate valve DN 400 (16 inch)

8

23/10/2018

4:00

23/10/2018

4:30

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ለመወዳደር ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡-

1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ ዓይነት በዘርፉ ለ2018በጀት ዓመት የታደስ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)፣ እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸው ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ለሎት 3 የማዕድን ማዘዋወርና ማስተላለፍ ፈቃድ ያለው መሆን አለበት።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው አድራሻ በቢሮ ቁጥር ብሎክ 2 በግንባር በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሶፍት ኮፒ( soft copy ) መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ግዥ የሚፈጽሙበትን 2% (2 በመቶ) በኢትዮጲያ ማአድን ኮርፖሬሽን ስም( Ethiopan Mineral Corporation) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች ከታወቀ በሶስተኛው ቀን በማስታወቂያ ቦርድ ይለጠፋል።

4. የጨረታ አሸናፊዎች ባስገቡት ዝርዝር መሰረት ገንዘቡን ከከፈሉበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለባቸው:: የጭነት ማጓጓዟ የማቅረብ ሃላፊነት የገዥ ይሆናል፤ ሎት 1 ላይ የተጠቀሰውን በሚመለከት ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት የማስወገጃ እውቅና የተሰጠው መሆኑን ወይም ቀጥተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው በዚሁም መሰረት እቃውን ሲጭኑም ይዘው ሲያጓጉዙ ለሚከሰተው ማንኛውም ነገር ገዥ ሙሉ ሀላፊነቱን ይወስዳል፤ እቃ የሚገኘው ሻኪሶ እና ቧንቧ ቅርንጫፍ ቢሮ ነው። የሎት 2 ዕቃ የሚገኝበት ቦታ አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት ላይ ነው፡፡ ሎት 3 ላይ የተጠቀሰው እቃ የሚገኘው ሻኪሶ ቅርንጫፍ ቢሮ ነው፤

5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

6. ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ሶስት ማህተም ያረፈበት በማድረግ በፖስታው ጀርባ ላይ የድርጅታቸውን ስም፤ የጨረታውን ሎትና ዓይነት ሙሉ አድራሻቸውን ጽፈው እና ፈርመው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

7. ጨረታው የሚዘጋው እና የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀን መሰረት ሲሆን የመዝጊያ እና መክፈቻ ቀኑ በበዓል ቀን ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

8. ተጫራቾች በሚሰጡት የዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) የማካተት ግዴታ አለባቸው ነገር ግን ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስን ካላካተቱ ኮርፖሬሽኑ ተጫራቹ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ቫትን ጨምሮይወሰዳል።

9. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ -22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ 

በስልክ ቁጥር 0911 622 263 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-30 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Mineral Corporation (EMC)
  • Buyer address: 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T11:40:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders