ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣ የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የማሸጊያ ፕላስቲክ፣ መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

CN/DE/02/18

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር በድርጅታችን አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የአይቲ ዕቃዎች፣የጽዳት ማሽነሪዎች፣ የማሸጊያ ፕላስቲክ፣ መጠረዣ ሪንግ ወ.ዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 300.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡00) ማግኘት ይቻላል።

ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ ቀጠሮ በማስያዝ ገርጂ በሚገኘው የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት፣ ቃሊቲ በሚገኘው ጃቲ የዕቃ ግምጃ እንዲሁም አማልጋ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ግምጃ ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ከጨረታ ዋጋቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋርንቲ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ዕለት ጠዋት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው

የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-156 9992

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-29 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000958158
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T11:50:52.000Z
  • Buyer website: https://commercialnominees.com/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders