የዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ. ኩባንያ የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተሽከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቅሪቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር (005/2018)

የዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ. ኩባንያ የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን ተሽከርካሪዎችና የተሸከርካሪ አካላት እና ሌሎችን ቅሪቶች ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተሽከርካሪዎቹን የተሽከርካሪ ቅሪት እንዲሁም ሌሎች ቅሪቶችን ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ቦሌ ኃይሌ እና ዓለም ህንጻ ሁለተኛ ወለል ከሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ስነድ በመግዛት አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሸዋ ዳቦ ወደ ቀኝ ገባ ብሎ በሚገኘው የኩባንያው የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆያ (RICOVERY) ውስጥ በማየት ከሰኔ 08 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2.00 ሰዓት እስከ 6.00 ሰዓት እንዲሁም ከሰዓት 7.00 ሠዓት እስክ 11፡00 ሠዓት ድረስ እሁድንም ጨምሮ እንዲሁም ስኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይቻላል።

1. ተጫራቾች ቅሪት ንብረቶችን እና ተሸከርካሪዎቹን ከሰኔ 08 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ እሁድንም ጨምሮ ቃሊቲ በሚገኘው የኩባንያው ሪከቨሪ ጊቢ ውስጥ በመገኘት ማየት ይቻላል።

2. ጨረታው ሀሙስ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት ተዘግቶ በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት ቦሌ ዓለም ህንጻ 2ኛ ፎት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4.30 ሠዓት ላይ ይክፈታል።

3. ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የመነሻ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) ዘመን ኢንሹራንስ ኩባንያ አ/ማ ወይም (ZEMEN INSURANCE S.C) ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ከቀረጥ ነጻ ከሆኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር በሌሎች ተሸከርካሪዎች የተሽከርካሪ አካላት ከጨረታው በፊት ዕዳ ቢኖር በኩባንያው ይሸፈናል፡፡ በጨረታው ለተካተቱት ንብረቶች ከጨረታው በኋላ ያሉትን ማንኛውንም ወጪዎች ገዥው ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።

6. ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

7. የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) 15% (አስራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላል።

8. አሸናፊዎች የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10(አስር) የስራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን ካልተረከቡ የጨረታው ውጤት የሚሰረዝ ሆኖ ከላይ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹንም ሆነ ሌሎች ዕቃዎችን ከሪከቨሪ በራሳቸው ወጪ ላይነጣጠሉ በአንድ ጊዜ ከፍለው በ10 (አስር) ቀናት ውስጥ ንብረቶቹን ከሪከቨሪ መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. የጨረታው አሸናፊዎች የስም ዝውውር እስከ ስድስት ወር ድረስ ማጠናቀቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህ ሳይሆን ቢቀር ለሚፈጠረው ማንኛውም ጉዳይ (ችግር) ኩባንያው ኃላፊነት አይወስድም።

11. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ፡- 0944-17-36-73 ወይም 09-11-97-95-88 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ.

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-25 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Insurance S.C.
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T12:34:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders