ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የቢሮ መገልገያ ኢኩፕመንቶች፣ ኮምፒዩተሮችና ተዛማጅ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የብረትና አልሙኒያም ቁርጥራጮች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ንብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮች የቢሮ መገልገያ ኢኩፕመንቶች፤ ኮምፒዩተሮችና ተዛማጅ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የብረትና አልሙኒያም ቁርጥራጮች) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ደንቦች፡-

1. ንብረቶቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት “ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት " አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-58-25/011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፣

2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አሰተዳደርና ሎጂሰቲክስ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች በምድብ (ሎት) ተለይተዉ ከተቀመጡት ንብረቶች የመረጡትን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 03፡30 ሰዓት በባንኩ ህንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው።

6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት፡፡ ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤

7. የጨረታ አሸናፊዉ ንብረቶቹን ከማስተካከል፤ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።

8. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል::

9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ አ.ማ.

Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-07-02 09:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Bank S.C.
  • Buyer TIN: 0004608547
  • Buyer address: Josef Tito Street
  • Published: Jun 14, 2026
  • Posted at: 2026-06-15T13:37:17.000Z
  • Buyer website: https://www.zemenbank.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders