በደ/ኢ/ክ/መንግስት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከለዩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኬብል ሲሆን እንዲወገድ ባቀረቡት መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ መለያ ቁጥር 007/ 2018
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ኢ/ክ/መንግስት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከለዩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኬብል ሲሆን እንዲወገድ ባቀረቡት መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅቶች/ግለሰቦች/የመንግሥት ተቋማት/
1. የዕቃው ዓይነት የኤሌክትሪክ ኬብል ነው።
2, ሽያጩ የሚከናወነው በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ንብረትነቱ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ነው።
3. አድራሻ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በወላይታ ዞን ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በማርካቶ ክፍለ ከተማ ፋና ቀበሌ ነው።
4. የኤሌክትሪክ ኬብል ዓይነት 3*70*35 mm2 የሆነ ብዛት በጥቅል ከ400 ሜትር በላይ ነው፡፡ ነገር ግን ተጫራች የአንድ ሜትርን ዋጋ ይጫረታሉ።
5. ተጫራች ዕቃውን ለማየት የሚፈልጉ ከሆነ እስከ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ድረስ በመቅረብ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየትኛውም በሥራ ቀን በሥራ ሰዓት ወደ ፋይናንስ ቢሮ ቀርቦ በመጠየቅ ማየት ይችላል።
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ዕቃው ባለበት ይካሄዳል፡፡ 16ኛው የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
7. ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡ በሌላ አማራጭ የሚቀረብ ተቀባይነት የለውም።
8. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተቋሙ ሀላፊ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በግብርና ኮሌጅ አካውንት ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን ማንሣት ይኖርበታል።
9. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁጥር 0465513984 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
በደ/ኢ/ክ/መንግስት የግብርና ቢሮ የወላይታ
ሶዶ ግብርና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-06-30
- Publishing entity: Wolaita Sodo Agricultural College
- Bid bond: 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/
- Published: Jun 15, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.