ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ. በስርጭት በሚዲያ ቴከኖሎጂ ማማከር ስራ እና በሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና የተሰማራ ሲሆን የ2018 (2025/26) በጀት ዓመትን ጨምሮ ለ3 ዓመታት (ከ2025/26 እስከ 2027/28) የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Description
የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዢ የተጫራች ጥሪ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ. በስርጭት በሚዲያ ቴከኖሎጂ ማማከር ስራ እና በሚዲያ ባለሙያዎች ስልጠና የተሰማራ ሲሆን የ2018 (2025/26) በጀት ዓመትን ጨምሮ ለ3 ዓመታት (ከ2025/26 እስከ 2027/28) የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
መስፈርት
በአካውንቲንግ እና ኦዲቲንግ ቦርድ (AABE) የተሰጠ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት, የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት በዘመኑ የታደሰ የስራ ፈቃድ፣ የድርጅቱን የስራ ልምድ እና የባለሙያዎችን መረጃ (Profile) የሚያሳይ ሰነድ ማቅረብ፣የቡድን ብቃት፡ የተመደበው የኦዲት ቡድን ሙያዊ መግለጫዎች፣ ተገቢውን የIFRS/ISA ሥልጠና እና እውቀትን የሚያሳይ ዝርዝር ሰነዶችን ማቅረብ የሚችል
የመጫረቻ ሰነድ
ተጫራቾች የፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ሰነድን በተናጠል በፖስታ በማሸግ እና የጨረታ ማስከበሪያ የ20,000 ብር ሲ.ፒ.ኦ ከቴክኒክ ፕሮፖዛል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኦዲት የሚደረገውን የድርጅቱን የሰነድ ብዛት እና አይነት ከድርጅታችን የፋይናንስ ክፍል ጠይቆ መረዳት ይችላል።
ዓላማ
ኦዲቱ የተቋሙን አማካኝ ብዛቱ 224 ቦክስ ፋይል የሆነ የገቢ እና ወጪ ሰነድ፡- የፋይናንስ አቋም፣ አፈጻጸም እና የገንዘብ ፍሰት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (IFRS) እና በአጠቃላይ ተቀባይነት ባለው የሒሳብ አያያዝ መርህ (GAAP) ለመንግሥት የታክስ ዓላማ መሠረት ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ሪፖርቱን ሰርቶ ማቅረብና ሙያዊ አስተያየት ለመስጠት የድርጅቱን የሒሳብ መግለጫዎች በገለልተኛ ደረጃ መመርመር ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩት መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጎን በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አንደኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ18/10/2018 ዓ.ም ሐሙስ ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0115-589185
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-25 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Fana Media Corporation
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T07:46:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.