በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና አገልግሎት በቅርበት ለመስጠት የጋራዥ ግልጽ ጨረታ አውጥቷል

Description

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት ስር ያሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን የጥገና አገልግሎት በቅርበት ለመስጠት የጋራዥ ግልጽ ጨረታ አውጥቷል። ስለሆነም በዘርፉ ልምድ ያላቸው እና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በሚከተሉት መስፈርቶች መሰረት እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1. የጨረታው አይነት

የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጥገና፡-

ቪ-8፣ ላንድ ክሩዘር ፣ ሀርድ ቶፕ፣ ኮብራ ስቴሽን ዋገን፣ ፕራዶ፣ኒሳን አልሜራ፣ሂኖ የጭነት መኪና፣ ሃይ ሩፍ ሚኒ ባስ፣ ሚስቲ ቡሽ ፣ ማህንድራ፣ ቢሾፍቱ እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች

2. የተጫራቾች መስፈርት

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው
  • የTIN ቁጥር እና የVAT ተመዝጋቢ የሆነ
  • ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የጥገና ፊቃድ ሰርኬፍኬት ያለው
  • በተሽከርካሪ ጥገና ስራ በቂ ልምድ ያለው
  • የስራ ማስረጃ እና የቀድሞ ደንበኞች ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3. የጨረታ ሰነድ መግዣ

የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አምስት መቶ ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር  ዳይሬክቶሬት መግዛት ይቻላል።

4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአንድ በማሸግ ዘወትር በስራ ሰአት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ለጨረታው ማስከበርያ አንድ መቶ ሺህ ብር በባንክ ሲፒኦ ከጨረታው ስነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

5. የጨረታ መክፈቻ

ጨረታውም ከቀኑ ስድስት ሰአት ታሽጎ በዛው እለት ከቀኑ ስምንት ሰአት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በአል፣ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በስምንት ሰአት ይከፈታል።

6. ማሳሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ ጥቅም ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

የጨረታ ሰነዶች ዘግይተው ከቀረቡ ተቀባይነት አይኖራቸውም።

አድራሻ፦ ሆሳዕና

ስልክ፦ 046 178 4632

ድርጅት: የማ/ኢ/ርዕ/መስተ/ጽ/ቤት

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-25
  • Publishing entity: ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 15, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders