በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉምሩክ ኮሚሽን አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 57/2018
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽና በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን።
በመሆኑም፦
1. በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቮሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡ ለተሽከርካሪ ሀራጅ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሽግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሊሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
3. በጨረታው ላይ የተሽከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።
4. ተጫራቾች የተሽከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
5. በዕቃና ተሽከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች ወይም ተሽከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. የዕቃና በተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ.ቁ 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ
|
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም
|
የጨረታው አይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ ቤት
|
የእቃ ሃራጅ
|
እስከ 15/10/2018 |
16/10/2018 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡ |
|
የእቃ ግልፅ
|
እስከ 16/10/2018 |
17/10/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሽከርካሪ ግልጽ |
እስከ 17/10/2018 |
18/10/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል። |
||
|
የተሽከርካሪ ሃራጅ |
እስከ 17/10/2018 |
18/10/2018 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል |
8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡-ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች / ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡
11. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ዉስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
12. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ፡
011-470-85 03
አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሠልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-06-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-06-25 10:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Kality Customs Branch Office
- Buyer address: ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T08:10:15.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.