በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥ/ጽ/ቤት የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች፣ የውስጥ ላስቲኮች፣ ያገለገሉ ፍላፖች፣ ያገለገሉ በርሜሎች፣ ከማሽኖችና ከተሽከርካሪዎች ላይ የተቀየረ ዘይት እና ልዩ ልዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 03/2018
በአብክመ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥ/ጽ/ቤት የተለያዬ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች፣ የውስጥ ላስቲኮች፣ ያገለገሉ ፍላፖች፣ ያገለገሉ በርሜሎች፣ ከማሽኖችና ከተሽከርካሪዎች ላይ የተቀየረ ዘይት እና ልዩ ልዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ግለሰብ፣ ማኅበራትና ድርጅቶች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች በጨረታው ዙሪያ ሊከተሉዋቸውና ሊያውቋቸው የሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር፡-
1. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው የመሳተፍ መብት አለው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከሰሜን ሸዋ ገጠር መንገድ ጥገና ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ገንዘብ ያዥ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የተለያዬ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች፣ የውስጥ ላስቲኮች፣ ያገለገሉ ፍላፖች፣ ያገለገሉ በርሜሎች ከማሽኖችና ከተሽከርካሪዎች ላይ የተቀየረ/የተቃጠለ ዘይት እና ልዩ ልዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን ዓይነት እና መጠን ዝርዝር መግለጫ ከሰነዱ ማግኘት ትችላላችሁ።
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ወይም የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ዝርዝር መሰረት የሁሉንም ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ውድድሩ በጥቅል ድምር መሆኑን ለመግለጽ ነው።
6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ውጤቱ በተገለጸ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ዋጋውን በመክፈል ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ መ/ቤቱ ሁለተኛውን የጨረታ አሸናፊ የመጥራት መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት ንብረቶች ውስጥ በተናጠል ዋጋ መሙላት አይቻልም።
8. ተጫራቾች ንብረቶቹን ባሉበት ቦታ ማለትም ደብረ ብርሃን ጠባሴ በሚገኘው መ/ቤታችን ሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መመልከት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ መሙያ መሰረት በአግባቡ ሞልተው በፖስታ በማሸግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።
11. የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
12. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለበለጠ መረጃ፡- 011-681-34-10/011-681-30-66 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የሰሜን ሸዋ ገጠር መንገዶች ጥገና ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-01 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: North Shoa Rural Road Maintenance Office
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 16, 2026
- Posted at: 2026-06-16T08:39:40.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.