የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን መድሃኒቶችን፣ ሪኤጀንቶችን እና የህክምና መሣሪያዎችን እንዲሁም ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች የማስወገድ የአገልግሎት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የሦስተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር - አ/ጤ/ጣ-003/2018

የአዋሬ ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉትን መድሃኒቶችን፣ ሪኤጀንቶችን እና የህክምና መሣሪያዎችን እንዲሁም ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች የማስወገድ የአገልግሎት ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች መድሃኒቶችን፣ ሪኤጀንቶችን እና የህክምና መሣሪያዎችን በጥራት ለማቅረብ እንዲሁም ጊዜ ያለፈባቸውን መድሃኒቶች ማስወገድ የሚያስችል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የ2018 ዓ.ም የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን አለባቸው 

2. ተጫራቾች በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግሥት ግዢ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በግልጽ የሚታይ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነጻ ስለመሆናቸው መልቀቂያ (ክሊራንስ) እና ሌሎች አስፈላጊ ዶክመንቶችን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር  በአዋሬ ጤና ጣቢያ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (ሲፒኦ) ብቻ ከዋናው የጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም የሲፒኦ ሰነድ በኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከላይ በተገለጸው ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት ይህ ማስታወቅያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

9. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ እንጂ በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም።

10. ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ሳይሰርዙ ፣ ሳይጨምሩ እና ሳይቀንሱ ለተጠቀሰው አገልግሎት ወይም ዕቃ ዋጋውን ብቻ በዋጋ መሙያው ላይ መሙላት አለባቸው ፤ ይህን ያላደረገ ተጫራች ከጨረታ ውድድሩ ይሰረዛል። 

11. ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት /VAT/ ማካተት አለባቸው።

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ  ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።

13. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞላው ነጠላ ዋጋ ነው።

14. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-አዋሬ አዋሬ ጤና ጣቢያ ንጋት ኮከብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፊት ለፊት 4ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 868 8278 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአራዳ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአዋሬ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-27 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Aware Health Post
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Jun 16, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T08:45:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders