የደ/ብርሃን ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግልፅ ጨረታ በሁለት ጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ፓምፕ ላይ የሶላር ሲስተም እቃ አቅርቦት እና ሙሉ ስራውን ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 16/2018

የደ/ብርሃን ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግልፅ ጨረታ በሁለት ጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ፓምፕ ላይ የሶላር ሲስተም እቃ አቅርቦት እና ሙሉ ስራውን ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ፡-

1. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ ኦርጅናሉንና ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል በመሙላት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የድምር ስህተት ካለ በአንድ መስመር በመሰረዝ ፖራፍ በማድረግ የተስተካከለውን በምርመራ አምድ ላይ በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል።

2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል በደ/ብ/ከ/የመ/ው/ፍ/አ/ድርጅት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

3. ተጫራቾች የሶላር ሲስተም ሙሉ ስራ ኮፒ እና ኦርጅናል በፖስታው ላይ በማለት በአግባቡ እና በጥንቃቄ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. የሶላር ሲስተም ሙሉ ስራ ጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ እና በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን 8፡01 ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ቴክኒክ ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው ለብቻው ቴክኒካል ሰነድ በማዘጋጀትና ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በሁለት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ወደ ተዘጋጀው ቴክኒካል ሰነድ ጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ በተገለፀው ግዜ ገደብ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታውን ማስከበሪያ ተጫራቾች የተጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 1% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ሆኖም በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዝ ተጫራች ያስያዘበትን ኮፒ በማድረግ በጨረታ ሰነዱ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. የሶላር ሲስተም ሙሉ ስራ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል።

8. አሸናፊው ድርጅት ወዲያውኑ ውል ይፈጽማል የውል ማስከበሪያ በአሸነፈበት ብር 10% ያስይዛል።

9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይቻልም፣ ሆኖም ራሳቸውን ማግለል ወይም ጨረታውን ማሻሻል ቢፈልጉ በፖስታ በማሸግ ከጨረታው ራሳቸውን ያገለሉ እንደሆነ ወይም ያሻሻሉበትን የጨረታ ሰነድ ማሻሻያ በማለት የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ተወዳዳሪዎች እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል ቢፈልጉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማመልከቻ በመፃፍና ሳጥን ውስጥ በማስገባት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ፡፡

11. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ወጪ ደ/ብ/የመ/ው/ፍ/አገ/ ድርጅት ቢሮ ማድረስ ይጠበቅበታል።

12. አሸናፊው ድርጅት ድርጅቱ በጠየቀው እስፔስፊኬሽን መሰረት እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል።

13. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

14. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።

15. አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-681-70-23 መጠየቅ ይችላሉ።

የደ/ብርሃን ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 14:01
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ እና በ16ኛው ቀን 8፡01 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-01 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ እና በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debre Berhan Water and Sewerage Service Bureau
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 16, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T08:55:07.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders