የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ያገለገሉ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ያገለገሉ ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
የጨረታው መነሻ ነጠላ ዋጋ በቁጥር |
የጨረታ መነሻ ጠቅላላ ዋጋ |
የጨረታ መ.ቁጥር |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ባዶ ኪስ የሲሚንቶ ወረቀት |
40,000 (በቁጥር |
9.00 (ጠኝ ብር |
360,000.00( ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ |
አ/አ/ከ/መ/ባ /ን/ማ 02/2018 |
30 ቀን |
ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 |
ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:30 |
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባለስልጣን መ/ቤቱ ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 በመምጣት ብር 200 በመግዛት በሃና ማርያም ሲሚንቶ ውጤቶች በሚገኘው የባለስልጣን መ/ቤቱ ፕ/ፅ/ቤት በመሄድ ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ።
2. የተጠቀሰውን ንብረት ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በኢንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ቀን ተብሎ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ሳር ቤት በሚገኝው በባለስልጣን መ/ቤቱ 3ኛ ፎቅ የንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 144 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾቹ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚያስረዳ ህጋዊ ሰነድ የነዋሪነት መታወቂያ ፓስፖርት ወይም ፋይዳ ምዝገባ ማያያዝ አለባቸው።
5. ጨረታው ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለስልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 144 ይከፈታል።
6. ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ከውድድር ራሳቸውን የሚያገሉ ወይም ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ማስክበሪያው ለባለስልጣን መ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
7. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀባቸው በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ መክፈል ይኖርባቸዋል።
8. ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ
ስልክ ቁጥር 011-372-8947
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-06-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-06-26 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa Road Authority
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jun 15, 2026
- Posted at: 2026-06-16T09:31:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.