በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለአገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አብክመ ሊቤምአ/B/ዉ/ጨ/ቁ /3/9/2018


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለአገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1.  በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሺ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5.  የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች (ሎቶች) አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የሚያስይዙት በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ከተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በግዥና ንብ/አስ /ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይም ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 7 የጨረታ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 3158፣ ፋክስ 058 320 1183፣ ፖ.ሳ.ቁ 965 ማግኘት ይቻላሉ።

የአብክመ ሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-06-30 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 15, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T09:31:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders