Disposal, scrap and surplus sales

የወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ ንብረቶችን (የተለያየ መጠን ያላቸው መስታወት ከነ ፍሬሙ፣ ላሜራ በር እና መስኮቶች፣ ጄኔሬተር፣ ፕላስቲክ ወንበሮች፣ ጎሮንዳዮ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች፣ ዛቢያ፣ አካፋ፣ አሸንዳ፣ መኪናዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ

የወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ ንብረቶችን (የተለያየ መጠን ያላቸው መስታወት ከነ ፍሬሙ፣ ላሜራ በር እና መስኮቶች፣ ጄኔሬተር፣ ፕላስቲክ ወንበሮች፣ ጎሮንዳዮ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የቤት ከዳን ቆርቆሮዎች፣ ዛቢያ፣ አካፋ፣ አሸንዳ፣መኪናዎች እና ሌሎች ዕቃዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች -

1. የጨረታ ሠነዱን ከወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ 2ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከግ/ን/አስ/ር/ዳ/ሬት 100 ብር በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

2. ሽያጩ የሚከናወነው በወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ግቢ በሚገኘው በአስተዳደር ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

3. ንብረቶቹን ማየት የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሠነዱን ከገዛ በኋላ ወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ግቢ ከሰኞ እስከ አርብ ድረስ በስራ ሰዓት ቀርቦ ማየት ይችላል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለእያንዳንዱ ዕቃ በተገለጸው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ንብረቱን በአራት ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ከፍሎ ማንሳት አለበት። ንብረቱን በተጠቀሰው ቀን ካላነሳ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

7. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስ.ቁጥር 046 551 2116

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ወላይታ ሶዶ


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት
  • Bid opening: 2026-07-01 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Wolayita Zone Finance & Economic Development Buearo
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jun 16, 2026)
  • Posted at: 2026-06-16T09:56:55.000Z
← Back to all tenders