በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ ያገለገሉ የተለያዩ አሮጌ ጎማዎች፣ ያገለገሉ አሮጌ በርሜሎች፣ ያለገሉ የተለያዩ አሮጌ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ አሮጌ ሞረዶች፣ ያገለገሉ አሮጌ ብረት ድስቶች እና ያገለገሉ የፕርንተር ቶነሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ

ብሔራዊ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ አሸጨ/001/አኩስፋ-2/2018 ዓ.ም

1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ጥቅል (ሎት-1) -ያገለገሉ የተለያዩ እሮጌ ጎማዎች፤ ጥቅል ( ሎት-2)፦ ያገለገሉ አሮጌ ባርመሎች፣ ጥቅል (ሎት 3) - ያለገሉ የተለያዩ አሮጌ ባትሪዎች፤ ጥቅል (ሎት-4)፡- ያገለገሉ አሮጌ ሞረዶች፤ ጥቅል( ሎት - 5) – ያገለገሉ አሮጌ ብረት ድስቶች እና ጥቅል (ሎት 6) ያገለገሉ የፕርንተር ቶነሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንከ ዋስትና /BID-BOND/፣ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር /supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታከስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል። የጨረታውን መከፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው፦

5.1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ።

ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85 / 09 30 85 64 15 / 09 40 20 94 64 

አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

6. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ የጨረታ የማስከበሪያ ዋስትና ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የዕቃው ርከከብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።

8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው።

9. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው።

10. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ

Tel- 09 40 20 94 64

ኃይል ውሃ

አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ

Tel: 09-91-14-94-85 / 09 30 85 64 15

አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ አ/አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን
  • Bid opening: 2026-07-01 17:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛ ቀን
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Sugar Industry Group
  • Buyer address: ካሳንቺስ ፣ ከንግድ ሚኒስቴር በስተቀኝ ገባ ብሎ ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ከኪያሜድ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ሕንፃ በስተጀርባ የሚገኘው 4ኛ ፎቅ ላይ
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 16, 2026
  • Posted at: 2026-06-16T10:07:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders