በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 46/2017

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች ሸያጭ የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፡ የመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ፣ ምግብ-ነክ ዕቃዎች፣ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሣይክሎች በግልፅና በሃራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ማንኛውም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

2. ማንኛውም የሞተር ሣይክል ተጫራች ዕድሜው 18 ዓመት የሞላው ኢትዮጵያዊ መታወቂያ በማቅረብ መጫረት ይችላል።

3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጫራቹ ስም የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን መውሰድ ይችላሉ።

4. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

5. ማንኛውም የሃራጅ ጨረታ ተጫራቾች ለመዋቢያና ለንፅህና መጠበቂያ 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ለኤሌክትሪክ ዕቃዎች 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሣ ሺህ ብር) እና ላገለገሉ ሞተር ሣይክሎች 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት ለእያንዳንዱ ኮድ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ማሠራት የሚጠበቅበት ሲሆን የአንድ ኮድ ብቻ አሠርቶ በመምጣት አንዱ ሳይሳካ ወደ ሌላው ኮድ አዛውሮ መጫረት አይችልም።

6. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የሥራ ሰዓት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (ስድስተኛው ቀን ግልፅ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት በአዲሱ መጋዘን ይካሄዳል፤ የሃራጅ ጨረታው የግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ ይካሄዳል፤ ነገር ግን የጨረታው ቀን እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይካሄዳል።

7. ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም።

8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ት ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።

10. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።

11. ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

12. ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው።

13. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል።

14. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046 212 5396
ጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-22
  • Publishing entity: Hawassa Custom Commission Branch Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published: Jun 17, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders