የደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ አነስተኛ ማሽነሪዎች እና የግብርና ሥራ ሊውሉ የሚችሉ ማሽኖች በሚገኙበት ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

በደቡብ ኢት/ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ የመንማሽኖችን ለተለያዪ ሥራ አገልግሎት ሊውሉ መንግሥተ ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በክልሉ የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ አነስተኛ ማሽነሪዎች እና የግብርና ሥራ ሊውሉ የሚችሉ ማሽኖች በሚገኙበት ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት አድራሻ ወላይታ ሶዶ በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በገጠር ቴክኖሎጅ ማስ/ማዕከል፣ እንስሳት ጤና ጥበቃ ላብ/ ማዕከል፣ ዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻ/ማዕከል፣ግብርና ሙ/ሥ/ኮሌጅና ዲላ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት በአካል በመገኘት ከላይ በኩል በተገለጹት አድራሻ አስቀድመው ማየት እና ሲመለከቱ ከጨረታ ሰነድ ጋር ልዩነት መኖሩን ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመዘጋቱ ከአምስት የሥራ ቀናት በፊት ለአገልግሎቱ ማሳወቅ አለባቸው። ይህን ሳያደርጉ የቀሩ ተጫራች ጨረታው ከታሸገ በኋላ ለሚቀርበው አቤቱታ መ/ቤቱ ምንም ምላሽ ለመስጠት አይገደድም።

3. በተሽከርካሪዎች/ማሽነሪዎች ጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን የተሽከርካሪ በሚገዙበት የጨረታ መግዣ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በደቡብ ኢ/ክ በፋይናንስ ቢሮ ስም በማቅረብ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታው ማስከበሪያው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

5. የአሽናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ጀምሮ አምስት ከሥራ ቀን በኋላ ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች CPO ተመላሽ ይደረጋል።

6. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በቢሮው በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የማይመለስ 300.00/ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በደ/ኢ/ክ/መ/ፋይ/ቢሮ አካውንት ቁጥር 1000574914985 በኢት/ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፑን ይዘው በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረብያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሀዝና በፊደል በመጻፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለበት ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።

8. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ/ ማሽነሪ ንብረት ዋጋ በአንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ CPO የተጨመረበት ሁለት በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 10/10/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 30/10/2018 ዓ/ም ማክሰኞ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት በቢሮ ለዚሁ ከተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ15ኛው ቀን 30/10/2018 ዓ/ም ማክሰኞ ዕለት ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ዘግይቶ የደረሰ ተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የሌለው እና ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው ጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።

10. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪና ማሽነሪ ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመክፈል ማንሳት አለባቸው፤ በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት CPO ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ ጨረታ ላይ ይውላል።

11. መ/ቤቱ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ግልጽ ያደርጋል።

12. አገልግሎቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Publishing entity: South Ethiopia Region Finance Bureau Public Procurement and Property Disposal Service
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 17, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders